ዓርብ 6 ኦገስት 2021
ጎጃም ክፍለ ሀገር
ጎጃም ክፍለ ሀገር
ጎጃም በሰሜን ምራብ ኢትዮጵያ የሚገኝና በአባይ ወንዝ ተከቦ የሚገኝ ባህር ዳርን ፍኖተ ሰላምን አገው ምድርን መተከልን ፓዊ ቆላ-ደጋዳሞትን፣ አቸፈርን ደብረ ማርቆስን ሞጣና ብቸና አውርጃዎች እና በነዚ ውስጥም ከ 35 በላይ ወረዳዎችን ይዞ የሚገኝ የራሱ ስርዎ መንግስት የነበረው ከፍለ-ሃገር ነው። ጎጃም ውስጥ ኣሉ ከሚባሉት ከተሞች እንደ ባህርዳር ፡ ደብረ ማርቆስ ፡ፍኖተሰላም ፡ቡሬ ፡ኮሶበር ፡ ዳንግላ ፡ቻግኒ ፡ አዴት ፡ መራዊ ፡ ሞጣ፡ ቢቸና፡ ደጀን ይገኙበታል ፡፡ ጎጃም እንደነ በላይ ዘለቀ ያሉ ጀግኖች መፈጠሪያ እንዲሁም የአባይ እና የጣና ባለቤት ናት ፡፡
ጎጃም የቅኔ ትምህርት በስፋት የሚሰጥበት ፡እንዲሁም እንደነ የፍቅር እስከ መቃብር ደራሲ ሀዲስ አለማየሁ (ዶ/ር) (1902- 1996 ) ኣ.ም አቤ ጉበኛ (1925 - 1972 ) ዮፍታሄ ንጉሤ(1897-1937 ) የመሳሰሉ የጥበብ ሰወችን አፍርታለች ፡፡ ጎጃም በጤፍ አምራችነት ከታወቁት የኢትዮጵያ ክልሎች ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል። ጎጃም ሌሎች እንደ ገብስ ስንዴ በቆሎ ባቄላ አተር ወዘተ የሰብል አይነቶችን በማምረትም ይታወቃል። ጎጃም የአባይ እና ሌሎች የበርካታ ወንዞች መነሻ ነው ።ጮቄ ተራራ በዚሁ ክፍለ ሃገር ይገኛል።
ጎጃም በአሁኑ ጊዜ ማለትም አገራችን የፌደራሊዝም ስርኣት ከተከተለች ወዲህ ከአራት አስተዳደር ዞን ተከፍሏል ።ሥስቱ ማለትም አዊ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም በአማራ ክልል ሲገኙ መተከል ቤሻንጉል ጉምዝ ክልል ተካቷል ።
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
አስተያየቶች (Atom)
ደብረ ገነት ነብዩ ኤልያስ ቤተ ክርስቲያን
የሊቃውንት መፍለቂያ! ደብረ ገነት ነብዩ ኤልያስ ቤተ ክርስቲያን በምሥራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤልያስ ወረዳ የሚገኘው ደብረ ገነት ነብዩ ኤልያስ ቤተ ክርስቲያን በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥ...
-
ጎጃም ክፍለ ሀገር ጎጃም በሰሜን ምራብ ኢትዮጵያ የሚገኝና በ አባይ ወንዝ ተከቦ የሚገኝ ባህር ዳር ን ፍኖተ ሰላም ን አገው ምድርን መተከልን ፓዊ ቆላ-ደጋዳሞትን፣ አቸፈርን ደብረ ማርቆስ ን ሞጣና ብቸና...
-
ዮፍታሔ ንጉሴ - ተወርዋሪው ኰከብ በጥበቡ በለጠ ************* * …..ባለቅኔ፣ መምህር ፣ ጸሐፌ ተውኔት ፣ ዲፕሎማት፣ አርበኛ፣ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ፣ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሔራዊ...
-
አንዳንዶች ‹‹የኢትዮጵያ ቅኔ ዩኒቨርሲቲ ነው›› ይሉታል። ምክንያቱም ተማሪው ከመምህሩ ጋር ሰምና ወርቁን እያስማማ ሲዘርፍ ማስተዋል በቦታው የዕለት ተዕለት ተግባር ስለሆነ። ሌሎች ደግሞ የፍቅር እስከ መቃብር ታሪክ እት...

