ጎጃም ክፍለ ሀገር
ጎጃም በሰሜን ምራብ ኢትዮጵያ የሚገኝና በአባይ ወንዝ ተከቦ የሚገኝ ባህር ዳርን ፍኖተ ሰላምን አገው ምድርን መተከልን ፓዊ ቆላ-ደጋዳሞትን፣ አቸፈርን ደብረ ማርቆስን ሞጣና ብቸና አውርጃዎች እና በነዚ ውስጥም ከ 35 በላይ ወረዳዎችን ይዞ የሚገኝ የራሱ ስርዎ መንግስት የነበረው ከፍለ-ሃገር ነው። ጎጃም ውስጥ ኣሉ ከሚባሉት ከተሞች እንደ ባህርዳር ፡ ደብረ ማርቆስ ፡ፍኖተሰላም ፡ቡሬ ፡ኮሶበር ፡ ዳንግላ ፡ቻግኒ ፡ አዴት ፡ መራዊ ፡ ሞጣ፡ ቢቸና፡ ደጀን ይገኙበታል ፡፡ ጎጃም እንደነ በላይ ዘለቀ ያሉ ጀግኖች መፈጠሪያ እንዲሁም የአባይ እና የጣና ባለቤት ናት ፡፡
ጎጃም የቅኔ ትምህርት በስፋት የሚሰጥበት ፡እንዲሁም እንደነ የፍቅር እስከ መቃብር ደራሲ ሀዲስ አለማየሁ (ዶ/ር) (1902- 1996 ) ኣ.ም አቤ ጉበኛ (1925 - 1972 ) ዮፍታሄ ንጉሤ(1897-1937 ) የመሳሰሉ የጥበብ ሰወችን አፍርታለች ፡፡ ጎጃም በጤፍ አምራችነት ከታወቁት የኢትዮጵያ ክልሎች ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል። ጎጃም ሌሎች እንደ ገብስ ስንዴ በቆሎ ባቄላ አተር ወዘተ የሰብል አይነቶችን በማምረትም ይታወቃል። ጎጃም የአባይ እና ሌሎች የበርካታ ወንዞች መነሻ ነው ።ጮቄ ተራራ በዚሁ ክፍለ ሃገር ይገኛል።
ጎጃም በአሁኑ ጊዜ ማለትም አገራችን የፌደራሊዝም ስርኣት ከተከተለች ወዲህ ከአራት አስተዳደር ዞን ተከፍሏል ።ሥስቱ ማለትም አዊ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም በአማራ ክልል ሲገኙ መተከል ቤሻንጉል ጉምዝ ክልል ተካቷል ።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ