ሐሙስ 29 ሴፕቴምበር 2022

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያን የአብነት ትምህርት ተማሪዎች

 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያ

የአብነት ትምህርት ተማሪዎች

(የቆሎ ተማሪጎጃም

ከደብረ ገነት ኤልያስ እስከ ዲማ ጊዮርጊስ የተደረገ የቆሎ

(የአብነት ተማሪዎችን) ሕይወት ይቃኛል፡፡

በጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን (Getu Temesgen)


የቆሎ ተማሪ Church Educators in Gojam - part 1



የቆሎ ተማሪ Church Educators in Gojam - part 2



የአብነት(የቆሎ)ተማሪ ሕይወት በጥቂቱ


የቆሎ ት/ት ቤት(የአብነት )ት/ት ቤት ማለት ምን ማለት ነው ?
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በዲ/ን ይነበብ መዝገቡ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡♥♥♥፡፡፡፡፡፡፡፡

የአብነት ትምህር በብዞቻችን ዘንድ የሚታወቀው በሁለት ስሞቹ ብቻ ነው ይህውም
♥የቆሎ ተማሪ(የቆሎ ት/ት) የሚለው እና የቄስ ትምህርት የሚሉትን በብዛት ሕብረተሰቡእ ይጠቀምባቸዋል ወይም ይታወቃሉ እነዚህ ሁለት ስሞች የተሰጡበት የእዬራሳቸው ትርጉምና እንድምታ ቸው ከግብር እና ከግብር ስም ጋር የተያያዙ እንጅ የትምህርቱን ምንነት አይተረጉሙም እየራሳቸው እንያቸው ፦

የቆሎ ትምህር (ተማሪ)
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡♥♥♥፡፡፡፥ማለት ፦በብዛት የአብነት ተማሪዎች ትምህርት የሚማሩት ከዘመድ ፣ከወገን ፣ ከሀገር(ከቀዬ) ርቀው እርሃቡን እና ጥሙን ታግሰው ነው ።ይህ ሲሆን ተማሪዎች የዕለት ምግባቸውን(ጉርሳቸውን) የሚያገኙት ከማሕበረ ሰቡእ በእንተ ስማ ለማሪያም እመ አምላክ ትቁምለዎት ብለው ለምነው ነው ።በዚህ ጊዜ ተማሪው ♥የሽብራ ቆሎ ፣የስዴ ቆሎ ፣ የባቄላ አሹቅ ፣ የገብሰ ቆሎ ፣ የአተር(የጓያ) ንፍሮ ወይም የእንጀራ አልያም የገብስ ወይም የስዴና የማሽላ እንጀራ በወጥ ወይም ደረቁን እንጀራ ወይም እንጂ የስዴ ዳቦ ብቻ የተገኘውን በአኮፋዳው(መያዣ ነው ከቄጠማ ወይም ከሰሌን) የሚሠራ አሁን አሁን እንኳ ወደ ፔስታል ተቀይሯል በአንድ ላይ አጠራቅሞ ያንን አድርቆ ወይም በዕለቱ ከልመና በኋላ የሚመገበው ይሆናል የተረፈውን አድርቆ በማጠራቀም የደረቀውን ይመገባል በአጠቃላይ ተማሪ የሚመገበው የደረቀ ነው ይህም የሚሆንበት ምክኒያት ከእርጥቡ(ከለምለሙ) የተሻለ የመቆየት እድለ ስላለው ነው ። በዚያ ላይ ከቤተ ሰቡም ሲወጣ የደረቀ እንጀራ(በተማሪ ዘንድ ኮቸሮ) ይባላል በከተሜው ሕዝብ ዘንድ ደግሞ♥ድርቆሽ ይባላል ይህን እንኳን ለአማርኛው አይመችም ድርቆሽ ማለት ለሣር ነው ። ይሁንና ብቻ ተምዬዋ የእኔ ሆድ በአጠቃላይ ምግቡ ደርቅ ነው ያም ሆኖ በንጽህ ውሃ የተዘፈዘፈ ጨው እንኳን የሌለበት ደርቁን እንጀራ ይመገባል ከሌለም ያገኘውን ♥ቆሎ ይመገባል በዚህ ምክኒያት ስያሜ መቼ እንዳገኘ ባይታወቅም ይህ ስም ከሚመገበው አመጋገብ ጋር ተያይዞ የቆሎ ተማሪ(ት/ት ቤት) በማለት እንጠራዋለን ይህ ግን የትምሕርቱን ጥልቀትና ምጥቀት የሚገልጽ አይደለም
2ኛው♥የቄስ ተማሪ(ት/ት ቤት) የሚለው ስም ነው
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ይህ ስም ደግሞ የግብር ስም ነው ተማሪው ተምሮ ሲጨርስ መጨረሻ ለያ የሚያገኘውን ሥልጣነ ክህነት የሚያመላክት ነው ።ይህውም ተማራው ትምህርቱን ሲማር ለግብረ ዲቁና የሚበቃበትን በቂ እውቀት ሲይዝ ዲቁና ይቀበል እና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በቅንነትና በትኅትና ፣በንጽሕና በቅድስና ያገለግላታል ከዚያም አባቶቹ ከደረሱበት ማዕረገ ክህነት ለመቀበል የክህነት ማዕረግ የሚያበቃውን ትምህርት ከያዘ በኋላ ቅስና ይቀበላል ስለሆነም ከዚህ የተነሣ የቄስ ትምህር(የቄስ ተማሪ) የምል ስም ተሰጠው ይህም ግብር እንጅ የትምህርቱን ሁኔታ የሚገልጽ ባይኖረውም የሠጀመሪያውንና በአባቶቻችን ዘንድ ከጥንት የሚታወቀውን አብነት የሚለውን ስያሜ አያስረዳም በመሆኑም የአብነት ትምህት የእራሱ የሆነ ትርጉምና ምሥጢር ያለው በመሆኑ የትምህርቱን ምሥጢርና ምጥቀት እንዲሁም የአባቶቻችንና የወድሞቻችንን ከፍተኛ ድካምና ችግር ያሳለፉበትን ዋጋ ያስቀራል እና ቀተገቢ ስም የአብነት ትምህርት(የአብነት ተማሪ) በማለት ብንጠራው መልካም ነው
ሦስተኛውን✈✞✞✔ትክክለኛው መጠሪያ ስሙ ግን ያለው ትርጉም የሚከተለውን ይመስላል
✔አብነት ማለት ምሥክር ማለት ሲሆን ተማሪው(ደቀ መዝሙሩ) ትምህርቱን በሚገባ ተምሮ ከቤተ ክርስቲያኒቱ የትምህርት ዘርፍ በአንድ መመረቅ ሲችል ❖አብነቱን ያዘ ይባላል ይህውም ምሳሌ አርዓያ ሆነ አስበ መምህራንን አገኝ ወይም የመምህርነት ሞያ አገኘ ማለትን ያጠቃልላል
በአጠቃላይ ከላይ ያየናቸው ስሞች ተማሪውን በአንድም በሌላም መግለጽ ቢችሉም ✈ዋናው ግን ሦስተቸኛው ነው ።እላለሁ

❖❖❖የቤተ ክርስቲያን የአብነት ትምህርት ይዘቶቹና የአስተምህሮ ሥርዓት
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡❖❖❖፡፡፡፡፡፡
❖በቤተ ክርስቲያናችን የማስተማር ሥርዓትና ሂደት አካሄድ የሚያሃላ የትኛውም የሳይንስ ወይም የፍልስፍና ትምህር ሲስተም(ዘዴ) እንደሌላት በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ
ከዚህ አንጻር ከእነዚህም የትምህርት ሥርዓታት ከፊደል ቆጠራ ጀምሮ እስከ መጨረሻው የዜማ ቁንጮ የድጓ እንዲሁም የመጽሐፍ ትሥህርት ድረስ የራሱ የሆነ የማሴተማር ዘዴና አካሄድ አለው ። ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ ሀገራችን ባለትልቅ ውለታና የሀገሪቱም የጀርባ አጥንት መሆኗን ማንም የማይከደው ሀቅ ነው ይህም ማለት
✡ፊደል ቀርጻ የፊደል ገበታ አዘጋጅታ ለሀገሪቲ ማበርከቷ ግልጽ ነውና
ከፊደል ቆጠራ ጀምርን ስንዘረዝራቸው የሚከተሉት ናቸው ።

✔ #1ኛ ፥ የንባብ ትምሕር ቤት
✔#2ኛ ፥ የዜማ ትምህርት ቤት
✔#3ኛ ፥የቅኔ ትምህርት ቤት
✔#4ኛ ፥ የቅዳሴ ትምህርት ቤት
✔#5ኛ ፥ የአቋቋም ትምህርት ቤት
✔❖6ኛ ፥የዝማራ መዋሥዕት ት/ት ቤት
✔♠7ኛ ፦የመጻሒፍት አንድምታ ትርጓሜ ትምህርት ቤት ናቸው ።

በእነዚህ ትምህርቶች ሥር እጅግ በጣም ዘርፈ ብዙ የሆኑ ትምህርቶችን አካተው የያዙ ሲሆን የመጀመሪያው ማለትም ንባብና ዜማ እንዲሁም ቅኔ ማወቅ(መቀኝት) የሁሉም የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ግዴታ ነው ምን አልባት ዜማ ስንል ሁሉንም ወይነት አይደለም ግን ለድምፅ መሰበር(መሸራሸት) የማያስችለውን ጽዋትኦ ዜማን ማለቴ ነው ።
ይህንን ያላወቀ ንባብን አቀላጥፎ የግዕዝን ንባብ ማለት ነው የማያውቅና ቅኔ መቀኝ አልያም በትንሽ ዘይቤን መስማት የማይችል ዲያቆን እና ቄስ በቤተ ክርስቲያናችን አገልጋዮች ይህ ያልተማረ መረር ካለም ማሃይም የምትጮኽውን የማታውቀው ማለታቸው አይቀርም በመሆኑም አንድ የቤተ ክርስቲያን አልጋይ በሥርዓት ያገለግል ዘንድ ጸዋትኦ ዜማን እና ቅኔን መቀኘት መቻል አለ።

ዮፍታሔ ንጉሴ - ተወርዋሪው ኰከብ

ዮፍታሔ ንጉሴ - ተወርዋሪው ኰከብ በጥበቡ በለጠ ************* * …..ባለቅኔ፣ መምህር ፣ ጸሐፌ ተውኔት ፣ ዲፕሎማት፣ አርበኛ፣ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ፣ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሔራዊ...