የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያን
የአብነት ትምህርት ተማሪዎች
(
ከደብረ ገነት ኤልያስ እስከ ዲማ ጊዮርጊስ የተደረገ የቆሎ
(የአብነት ተማሪዎችን) ሕይወት ይቃኛል፡፡
በጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን (Getu Temesgen)
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያን
የአብነት ትምህርት ተማሪዎች
(
ከደብረ ገነት ኤልያስ እስከ ዲማ ጊዮርጊስ የተደረገ የቆሎ
(የአብነት ተማሪዎችን) ሕይወት ይቃኛል፡፡
በጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን (Getu Temesgen)
ጎጃም የቅኔ ትምህርት በስፋት የሚሰጥበት ፡እንዲሁም እንደነ የፍቅር እስከ መቃብር ደራሲ ሀዲስ አለማየሁ (ዶ/ር) (1902- 1996 ) ኣ.ም አቤ ጉበኛ (1925 - 1972 ) ዮፍታሄ ንጉሤ(1897-1937 ) የመሳሰሉ የጥበብ ሰወችን አፍርታለች ፡፡ ጎጃም በጤፍ አምራችነት ከታወቁት የኢትዮጵያ ክልሎች ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል። ጎጃም ሌሎች እንደ ገብስ ስንዴ በቆሎ ባቄላ አተር ወዘተ የሰብል አይነቶችን በማምረትም ይታወቃል። ጎጃም የአባይ እና ሌሎች የበርካታ ወንዞች መነሻ ነው ።ጮቄ ተራራ በዚሁ ክፍለ ሃገር ይገኛል።
ጎጃም በአሁኑ ጊዜ ማለትም አገራችን የፌደራሊዝም ስርኣት ከተከተለች ወዲህ ከአራት አስተዳደር ዞን ተከፍሏል ።ሥስቱ ማለትም አዊ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም በአማራ ክልል ሲገኙ መተከል ቤሻንጉል ጉምዝ ክልል ተካቷል ።
የሊቃውንት መፍለቂያ! ደብረ ገነት ነብዩ ኤልያስ ቤተ ክርስቲያን በምሥራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤልያስ ወረዳ የሚገኘው ደብረ ገነት ነብዩ ኤልያስ ቤተ ክርስቲያን በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥ...